የኢትዩጵያ ፖለቲካዊ ማዕከል ማነዉ?
በንጉሳዊ ስርዓት
የፖለቲካው ማእከል ከአገሪቱ Periphery/ጥግ ለሚመጡ ሃሳቦችም ግለሰቦችም እጁን ዘርግቶ እየተቀበለ እስከ 1960ዎቹ ቆይቷል። በዚህም ጊዜ የኦሮሞ አርበኞችን ሆነ ሌላዉን ብሄር ብሄረሰብ ከሁሉም የኢትዮጵያ ጥግ አምጥቶ የሚያከብር የፖለቲካ Frame Work ያቋቋመ ንጉሳዊ ሰርአት አንብሮ መቆየቱ ይታወሳል።
የ50አመቱ ፖለቲካዊ ማእከል እንዴት ይታያል?
1. የደርግ ሰርአት
ኢትዮጵያዊነት በነገስታቱ ሰርአት ሃቀኛ የነበረ እና ሁሉም ጥግ ያለውን ኢትዮጵያዊ በመልካም የሚመለከት በተቻለውም መጠን ወደ ማእከል የሚስብ መሆኑን ከወለጋ፣ ከሃረር፣ ከጅጅጋ ፣ከአክሱም ፣ከጎንደር ፣ከአፋር ወደ ማእከል መጥተው ከፍተኛ ትምህርታቸውን በውጪ ሃገር በንጉሱ ላኪነት ተምረው የመጡ Scholars ማየት በቂ ማረጋገጫ ነው። ቀድሞ እንደተጠቀሰው በሸዋ ላይ አማራ፣ በኦሮሞ መስፋፋት የመጣው ቱለማ እና የጉራጌ ማህበረሰብ የሸዋን Elite ወይም የሸዋ ማእከላዊ ፖለቲካን ቢያደራጅም ለአፄ ሃይለስላሴ መውረድ ትልቁን ሚና የተጫወተው የቱለማ Elite በንጉሱ መውረድ ማግስት መላውን የሸዋ አማራ elite አሳዶ በመግደል ሃብቱን በመዝረፍ የትርፍ ቤትና መሬት ለዓራሹ አዋጅን ተጠቅሞ በማደህየት የሸዋን አማራ አይኖችን አጥፍቷል። የሸዋ አማራ ለመላው አማራ palace Politics Agency ሆኖ ሲያገለግል የቆየ በመሆኑ የሸዋ መመታት መላዉን የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲያጋጥመው ሆኗል። Geographic periphery የነበሩት ማለትም ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ከማእከላዊ ፖለቲካ ባለቤትነት ተገፍተው political Periphery ሆነዋል። ይህም ማለት ሸዋ አማራ በተመታ ማግስት የሰሜ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ የአማራ ግዛቶች ያለተከላካይ ለጠላት እጃቸውን ታስረው እንዲሰጡ ሆኗል። በዚህም ከፍተኛ የቱለማ Elite Based በሆነው የደርግ ስርአት እና የወያኔ ታጋዮች አርጩሜ በላያቸዉ ላይ እንዲያርፍ ሆኗል። ይህ አዲስ Political Centrist በሸዋ አማራ Elite መቃብር ላይ መፈጠሩ መላው አማራ Political Agency ማጣቱ እና እንደ ማህበረሰብ ሰብሳቢ አባት ለማጣቱ ምክንያት ሆኗል። ይህ የቱለማ elite ሃይል ለperiphery እጅግ ንቀት ያለዉ በመሆኑ እና ከገበርክ ገብር ካልሆነ ትቃጠላለህ የሚል አቋም በመኖሩ እንደ ሃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ ከጥግ/ Periphery ለመጡ ኦሮሞዎች እንኳን ርህራሄ አልነበረዉም። ግለሰቦቹን ወደ ስልጣን ለመምጣት ኦሮሞነታቸውን ቢጠቀሙበትም ፣መላውን በጥግ የሚኖር ኦሮሞ የማዕከል ተጠቃሚ እንደውም አጋር ሆኖ እንዲወጣ በማሰባቸው ምክንያት ብቻ በቱለማ elite ሰይፍ እንዲቀጡ ሆኗል።
በ1967 የተፈጠረውም የወያኔ ሃይል የኮሚኒስት አይዲዮሎጂ በመሸከም ተወልዶ የባላባት ፖለቲካ ውስጥ ያለውን የትግራይ ሃይል በመደምሰስ ጫካ በመግባት የCommunist Anti-Bourgeois thesis ሃሳብ ተግብሯል።ነገር ግን በተገንጣይ ሻቢያ እና በቱለማው elite የሚቀነቀነውን Anti-Amhara narrative በደንብ ሲሰነጠቅ Anti-Shewan Amhara Elite ideology ፖለቲካ በማራመድ የደርግ ስርአት አሸንፎ የመጣውን የቀ/ሃይለ ስላሴ መንግስት በሌለበት ታግሏል፤ ነገር ግን ይህ አዲስ Political Centrist ወይም የቱለማ Elite ሃይል ትግራይን እንደ Periphery የሚያይ በመሆኑ ስልጣን በያዘ በሁለተኛው አመት በተመሳሳይ Communist መስመር የተቀመጠውን ወያኔ እና የትግራይ ህዝብ ጦርነት ከፍቷል። ታሪክ ራሱን ደገመ በሚባል ደረጃ በአብይም ጊዜ ያኔ ተገንጣይ አሁን ጁንታ በሚል Code Word ጦርነት ከፍቶበታል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እጅግ ደካማ የፖለቲካ አረዳድ የነበረው የኤርትራ እና የትግራይ ሃይል አማራ ጨፈጨፈኝ ብሎ ያስብ ነበር አሁንም ቢሆን ከደርጉ ጊዜ ያልተማረው የትግራይ ሃይል ለሁለተኛ ጊዜ በተመሳሳይ አብዮታዊ ደሞክራሲ አስተሳሰብ የተሰለፈው የቱለማ Elite አማርኛ እየተናገረ አስርቦታል አስሮታል ወግቶታል። ይሁንና የአማራን ህዝብ በመክሰስ ከገዳዩ ጉያ ዉስጥ ገብቷል።
Political Periphery በመሆኑ ምክንያት ዝቅተኛ የሚባል አገራዊ ፖለቲካ አረዳድ ያለው የትግራይ ፖሊቲ አማራ ጨፈጨፈኝ ብሎ አውጇል። ለዚህም ፋኖን በሃሰት ከሷል። ሃሳቡን ለመፈተሽ ያክል ባለፉት ሁለት አመታት የፌደራል መንግስቱ ሶስት ጦርነት ያደረገ ሲሆን በመጀመሪያው ጦርነት ትግራይ መግባቱ ይታወሳል። በዚህም ወቅት የፋኖ አደረጃጀት አለመፈጠሩ እና በሚቀጥሉት ሁለት ጦርነቶች ማለትም በአማራ ክልል ብቻ በተደረጉት ህዝባዊ አማራ ፋኖ መቋቋሙ ማስረጃ ይሆናል። በ Proper Tigray ዉስጥ ለተደረገ ጦርነት ሊያዉም ከወራቶች በኳላ የተፈጠረዉ ፋኖ በማይታጠቃቸዉ mechanized Armaments ለደረሰበት ጥቃት ፋኖን እንደ ጨፍጫፊ መክሰሱ የትግራይ ፖለቲካ እጅግ ፈሪ እና የአረዳድ ችግር እንዳለበት ያሳያል። በደርግ ጊዜ የሰራውንም Political Mistake መድገሙ ለሁለተኛ ጊዜ በቱለማ elite ጦርነት ደጋሽነት እንዲለበለብ ምክንያት ሆኗል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ Political Centrist ማነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያልቻለ የትኛውም ሃይል ወደ ማእከላዊ የኢትዮጲያ ፖለቲካ መምጣት እንደማይችል ጸሃፊው ይመክራል።
2. የቱለማ Elite መገለጫዎች
የቱለማ Elite የጥቅም ኢትዮጵያዊነት (ሌሎችን ያገለለ) Resource Centralization ላይ የተመረኮዘ እና የአማራ ጠል ጽንፍ ፖለቲካ መገለጫዎቹ ናቸው።
2.1 የጥቅም ኢትዮጲያዊነት
ይህ ሃይል የሸዋን አማራ Political & Economic Class በስውር አጥፍቶ አማራ መስሎ የሚንቀሳቀስ ልክ እንደ ወርቅ ቅብ ያለ ሃይል ነው ይህንንም የሚያደርገው ለስልጣን መቆያ እና በጎበና ዳጨ በኩል ተጠግቶ የነበረውን የንጉሳዊ ስርአን ለመምሰል በመሞከር ነው። በዚህም እንቅስቃሴው በመላው ኢትዮጵያዊ ፣ አማራ መስሎ እንዲታይ ያደርገዋል። በዚህም ምክንያት ይህ ሃይል ለሚፈጽመው በደል ሁሉ አማራው በመቀጮ ወንበር ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል። በደርግም ጊዜ ይሁን አሁን ስንመለከት የነገስታቱን ሃውልት የሚያሳምር ነገር ግን ነገስታቱን ቀን በቀን ሲያዋርድ የሚውል ፖለቲካ ማራመዱ ቀላል ማሳያ ነው። አላማዉም ከላይ አማራ መስሎ ለመታየት የሚደረግ Political Convince & Confuse ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ሃይል ከተለያየ አካባቢ ስልጣኑን የሚገዳደር በተለይም ከጥግ/Periphery ለመጣ መላውን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው የሚል ነጋሪት በመጎሰም ሰብስቦ ወደ ጦር ሜዳ የሚልክ ከመሃል ሸዋ አማራ ከመጣ ደግሞ በሴራ የሚያጠፋ ሲሆን በቅርቡም ኢትዮጵያን ለሺህ አመታት የጠበቀው የአማራ ህዝብን እንደ ሃገር በታኝ ስሎ ብሄር ብሄረሰብን ለማዝመት ሲጥር ተመልክተናል። አብዛኛው የቱለማ Elite ከመንግስቱ ሃ/ማሪያም እስከ አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያዊነትን ለእኩይ አላማ ተጠቅመውበታል።
የአብይ አህመድ የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ አመራሮች 85% በቱለማ Elite የተያዘ መሆኑ ከደርግ ጊዜ ከነበረው ሰርአት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ያደርገዋል። የወለጋ Elite የሆኑትን እነ ሃይሌ ፊዳን የበላበትን መንገድ በአብይ አህመድ ስርአትም ለስልጣን መውጫ የተጠቀመውን የወለጋ Elite, bystander ማድረጉ የነገሩን ተመሳሳይነት ያሳብቃል። ይህንንም ሲያደርግ በአማራ ካባ መሆኑ ከወለጋ ለሚመጡ የፖለቲካ ሃይሎች እንደ ነፍጠኛ እንዲስሉት ሆኗል። ከደርግ ስርአቱ ባልተለየ የኪነጥበብ ፣ በሆድ የተገዙ ፖለቲከኞችን ፣ጋዜጠኞችን እና የእምነት ሰዎችን በዙሪያው ሰብስቦ የጥቅም ኢትዮጵያዊነትን ሲያራምድ ይስተዋላል። እንደ ማሳያም ሌንጮ ለታ ፣ ዳንዔል ክብረት እና አብርሃም በላይን በጥቅሙ ሰንሰለት ውስጥ እናገኛቸዋለን።
ይህ ሃይል ፣ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴን ከአማራዉ ህዝብ የተፋቱ ለማድረግ ሁለት ካርዶችን የሳበ ሲሆን በግዜዉ መሬት ላራሹ አዋጅ ለምን እንኳን እንደፀዳቀ ያልተረዳዉ ፣ አማራ ጨቋኝ ነዉ ብሎ የተሰለፈዉ ግልብ ደርጋዊ የአማራ elite ዛሬም በአዲስ ስሙ በዓዴን ሆኖ እናገኘዋለን፣ ለማረጋገጫዉም በ1986 የብዓዴን manifesto ላይ በሰፊዉ የአማራን ነገስታት ማዉገዙ ያልተቋረጠ ተላላነትና አማራ ሆኖ የአማራን መሰረት የሚነቀንቅ elite በዉስጣችን ስለመኖሩ ማሳያ ነዉ።
2.2 የወሎ እና ትግራይ ርሃብ: አማራዉን በንጉሱ ላይ ለማስነሳት ብሎም ንጉሳዊ ስርዓቱን ለመገርሰስ ታስቦ ፣ከንጉሱ እዉቅና ዉጪ በሴረኛዉ ቱለማ elite ማህበረሰቡ ታፍኖ man-made Hunger እንዲፈጠር ሆኗል ፣ በጣም የሚደንቀዉ በ60 ኪሜ ርቀት በቂ የሰብል ምርት መኖሩ ነበር። ንጉሱም አካባቢዉን ከጊዜ በኳላ ጎብኝተዉ እጅግ አዝነዉ ነበር። የሚደንቀዉ ንጉሱን ከማስጠላት አልፎ የሺ ዘመናት ትሩፋት የሆነዉን monarchy ጭራሹኑ ለማፍረስ መጠቀማቸዉ ነበር። እንደ ማረጋገጫም በንጉሱ ዙርያ የነበሩት የሸዋ አማራ elites ተከሰዉ የተረሸኑት በዚሁ በሴራ በተፈጠረ ረሃብ ነበር። በመጨረሻ ግን ሃቀኛዉ ርሃብ ከ ቀ/ሃይለ ስላሴ መዉረድ አስር አመት በኳላ አማራዉን ጎበኘ ፣ቀድሞ እንደተደረገዉ አንድም የደርግ አባል በዚህ ረሃብ ምክንያት አልተጠየቀም።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ የድርቅና ርሃቡን አካባቢ ለመጎብኘት እና መቅሰፍቱን ለማየት ዕድል አላገኙም። እንደ ማንኛውም ሕዝብ ጆናታን ዲምቢልቢ የሠራውን ፊልም መስከረም 1 ቀን 1967 እንዲያዩ ነው የተገደዱት። ከሥልጣን ከመውረዳቸው ሦስት ይሁን ስድስት ወር በፊት የወሎ ክፍለሃገርን በእንደራሤው በደጃዝማች ሰለሞን አማካኝነት ሲጎበኙ አገሩ በሙሉ የጥጋብ አስመስለውና ፍፁም ረሃብ የሌለበት አድርገው ነበር ያስጎበኟቸው። ሰው ግን በርሓብ ከቀዬው መፈናቀል ጀምሮ ነበረ ። ንጉሡ ሆን ተብለው ስለርሃቡ እንዳያውቁ ተደርገዋል። ደጃዝማች ሰለምን ማለት ደግሞ፣ የኢሣያስ አፈወርቅ አጎት ናቸው! ንጉሡ ስለርሃቡ እንዳወቁ የሣውዲ መንግስት በግል የሰጣቸውን 5 ሚሊየን ዶላር በርሃቡ ለተጎዱት መለገሳቸው ተገልጿል።
ከብዙ ጉዳዮች እንደ ዋነኛ ነጥብ ሆኖ ስለርሃቡ ኃላፊ የሚሆን ሰው ለማግኘት፣ ንጉሡ በባለሥልጣናት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ኮሚሽን አቋቁመው ነበር። ይህ በፕ/ር መሥፍን ወ/ማሪያም የሚራው የመርማሪ ኮሚሽን 98% ተመርማሪዎችን ነፃ አድርጓቸዋል። ሁለት ሰዎችን ብቻ ነው ይከሰሱ ነበርያላቸው። ይከሰሱ ማለት ደግሞ ጥፋተኛ ናቸው ማለትም አልነበረም። ደርግ እና የፕሮፌሰሩ ጥምረት ግን ሁሉንም ያለ ፍትህ ጨፍጭፏቸዋል።
እንደ ማነፃፀሪያ በ1967 ዓ.ም 250,000 ሕዝብ ተራበ ተብሎ አገር ይያዝልኝ ብሎ በጋራ ያበደ ልሒቅ ነበር። ያውም ትርፍ ምርት በነበረበት ሁኔታ። ከአሥር ዓመት በኋላ 1977 ዓ.ም. ላይ 14 ሚሊየን ሕዝብ ሲራብ ግን ይኽው ልሒቅ በአርምሞ አልፎታል። ስለዚህ የ1967 ዓ.ም የተራብን ፕሮፓጋንዳ ዓላማው ምን እንደነበር ለራሱ ግልፅ አድርጓል።
2.3 የበላይ ዘለቀ ስቅላት፣ ታሪክ እንደሚያስታዉሰን ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ አፄ ሃይለ ስላሴ በእንግሊዝ እርዳታ ደ/ማርቆስን ነፃ ሲያወጡ በላይ ዘለቀ ጦሩን አሰልፎ የተቀበላቸዉ ሲሆን በንጉሱም እጅግ ተወዳጅ ነበር። ንጉሱ ኢትዮጵያ ሲገቡ ባንዳዉም አርበኛዉም በአንድ ተሰልፎ እንደ ጀግና ስልጣን ተቀበለ። ከበላይ ጋርም በቀድሞ የሚተዋወቁ ባንዳዎች እሱን ለማጥፋት ነገር ሲጎነጉኑ ኖረዉ ፍትጊያዉ በጀግናዉ በላይ መሰቀል ተጠናቀቀ። ይህንን ክስተት በ ንጉሱ ላይ የተመረረ የ አማራ ወጣት ለማነሳሳት የቱለማዉ elite ተጠቀመበት ግልብ የሆነዉ ደርጋዊ፣ኢህአፖዊ elite በደምብ የጉዳዩን ሚስጥር ሳይረዳ በንጉሱ ላይ አሴረ፣ በመጨረሻም ከ በላይ ዘለቀ አንጋች የተወለደዉ ኮ/ል አጥናፉ አባተ ቀ/ሃይለ ስላሴን በመግደል የአማራን የመከራ ግዜ አስጀመረ። የቱለማዉ elite ግልብ የሆነዉን ደርጋዊ የአማራ ሃይል በደምብ ሲጠቀም ከቆየ በኳላ አጥናፉ አባተንም በጠራራ ፀሃይ ገድሎ ጣለ። ይህ ታሪክ ራሱን ደግሞ የቱለማዉ elite የተለመደዉን የፖለቲካ ሴራ ከ ደርጋዊ፣ኢህአፖዊ elite extension በሆነዉ ብዓዴን ረዳትነት በሰኔ 15 እንቁ የአማራ ጀግኖችን ረሽኖ አማራዉ አማራን ገደለ የሚል ትርክት መንዛት ጀመረ፣ በአሁኑ ግን የአማራዉ ወጣት በደርግ ግዜ ከነበረዉ እጅግ የተሻለ በመሆኑ ለቱለማ ፖለቲካዊ ሴራ ጀርባዉን ሰጠ። ዛሬ ላይ የአማራን ህዝብ በንጉሱ ላይ ለማስነሳት የተጠቀሙበትን ወሎ እና ደ/አ በላይ ዘለቀ የኦሮሞ ናቸዉ በማለት የቱለማዉ ሃይል በየመገናኛዉ ብዙሃን መለፈፍ ጀመረ። ትናንት የአማራዉን ስር ለመንቀል ንጉሳዊዉን ስርዓትን ሲከስ የነበረዉ አሁን ላይ የአባገዳ ስርዓትን ተቀበሉ ይለናል። ፀሃፊዉ እንደሚያስረዳዉ በትግራይ ሃየሎም አርዓያን የበላዉ ህዉሃት ለትግራይ ህዝብ አሁንም ለምን የልብ ትርታ ያክል ተፈላጊ እና ተወዳጅ እንደሆነ አንባቢዉ ይረዳ።
3. የቱለማ Elite በአማራ ጠል ጽንፈኝነት ውስጥ
ይህ የቱለማ Elite ካባ እጅግ አደገኛ እና ዋና ባህሪው ሆኖ እናገኘዋለን በጎበና በኩል ከነገስታቱ ስር ሆኖ የነገስታቱ እጅግ Established መሆን ሲያንገበግበው መኖሩን በሚያሳይ መልኩ ዋና Target አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ባህል ፣ቋንቋ እና ኢኮኖሚን ነው። በደርግ ስርአት መግቢያ ማግስት የሸዋን አማራ ቀጥሎም በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የአማራ Elites መጨፍጨፉ ለዚህ ማሳያ ነው ከዛም ባለፈ አማራ የሚባል ህዝብ የለም የሚል እጅግ አስደንጋጭ የሆነ Genocidal Agenda በድፍረት በደርግም ይሁን በአብይ ጊዛዜ መንጸባረቁ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል። ለዚህም ለስልጣን ብቻ የሚፈልገውን የወለጋ Elite አማራ መጣብኝ ፣ዘመተብኝ ፣ ያልተዳከመ አማራ ለኦሮሞ ስጋት ነዉ በሚል Narrative Lobby አድርጎ አማራን በወለጋ እንደጨፈጨፉ አድርጓል። ለዚህም እንደ ማሳያ የራሱን ሸኔ የተባለ ሃይል መንግስት በስውር የሚመራው በቅርቡም በWashington Post በስፋት የተፃፈለት የጃል ፈቀደን ሠራዊት እንደማሳያ ማስቀመጥ ይቻላል። አላማውም ተቀናቃኝ የሆነውን የሸዋ አማራ እና መላውን የአማራ ህዝብ በተገኘበት በመግደል የስልጣን ጥያቄ እንዳይኖረው ብሎም በህልውና አደጋ ውስጥ እንዲዛክር አድርጎታል። በአብይ መራሹ ስርዓት ሌላው አስደንጋጭ እንቅስቃሃይል : በጀዋር መሃመድ ከአመታት በፊት የተገለፀውን “ኢትዮጵያ እኛን ካልመሰለች በትነናት እንሄዳለን” የሚለውን ሃሳብ በሰፊው እየተገበረው ይገኛል። የኦሮሚያ Republic ለማንበር ኢትዮጵያን Confederate በማድረግ ለማሳካት ትልም አድርጎ ይንቀሳቀሳል። ለዚህም አማራው የኦሮሚያ ካርታ እውን ለማድረግ Threshold በሆኑት ማለትም ከወሎ-መተከል-አዲስ አበባ -ደራ -ወለጋ እና ከሚሃይል ላይ ይጨፈጭፋል ብሎም የአማራ ህዝብ Concentrated ከሆነባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እንዲበተን ይደረጋል።
ይህን እንቅስቃሴ በደርግ ጊዜ የተሳካለት የታጠቀውን እና የተደራጀዉን አማራ በመሬት ላራሹ አዋጅ በመበተን የተጀመረው ስራ አሁን ላይ ያልታጠቀ እና ደሃ የሆነውን አማራ በማፈናቀል The Oromo National Project ቀጥሏል። ሌላዉ በትርፍ ቤት አዋጅ ከአዲስ አበባ እና ዙሪያው ሲሳደድ የነበረው የተሳካለት አማራ ነበር አሁን ላይ ደግሞ ደሃ የሆነው አማራ በሸገር ከተማ Project እና የጨረቃ ቤት በሚል ሰበብ እየተፈናቀለ ይገኛል። ኢትዮጲያ Federal የሆነች አገር በመሆኗ ስልጣን ለብሄር፣ብሄረሰብ እና ህዝቦች ዉክልና ተሰጥቷል። የመሬት ባለቤትነት የብሄር ብሄረሰብ እና ህዝቦች የጋራ ሃብት ሆኖ በአንቀፅ 40/3 ላይ እናገኘዋለን ይህም ማለት የእገሌ የሚባል መሬት አለመኖሩን በህግ ያረጋግጥልናል። ታዲያ በፈደራሊዝም በቂ የአስተዳደር ወሰን ያለውን የኦሮሚያ ክልል እስከ ጎጃም/መተክል እና ከሚሴ/ወሎ በማስፋት አገሪቷን ወደ Confederate ወስዶ መሬትን ለአንድ ብሄር ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ይህ ሃይል በህዋሃት ፊታውራሪነት አንቀፅ 39ን ባላከበረ መልኩ ተመሳሳይ ቋንቋ የማይናገሩ ማህበረሰቦችን እና ስምምነት የሌላቸውን በአንድ ኦሮሚያ ክልል በሚባል ማስቀመጡ አላማው ለአማራው ተገዳዳሪ ሃይል በማበጀት በኦሮሞው እና በአማራው አለመስማማት ውስጥ ከአናሳ የብሄር ቁጥር የመጣው በብሄር ፈደራሊዝሙን Technically መጠቀም ለማይችለው የትግራይ ሃይል እንደ ስልጣን ማስጠበቂያ ቢጠቀምበትም አማራውን እንዲያጠቃ እንዲያደክም በህዋሃት እርዳታ ያደገው የኦፒዲኦ ሃይል ትግራይን ብሎም ህዋሃትን በእሳት በማቃጠል ተጠናቋል።
4. የቱለማ Elite እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ይህ ሃይል ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከነገስታቱ በተለየ መልኩ ተጣብቆበት ይገኛል ይህን እምነት ለስልጣን ማስጠበቂያ ይጠቀምበታል ከዛም ባለፈ አለም አቀፉ የሆነውን እምነት የግሉ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ ማየታችን ብዙም አያስገርምም ነገር ግን ይህን እምነት ከአማራው ጋር ሆን ብሎ በማስተሳሰር አሁንም በተለመደው መልኩ አማራው በሌለበት የችግሩ ገፈት ቀማሽ ያደርገዋል። እጅግ ሙስሊም ጠል ለመሆኑ ማሳያም በነዚህ Elite በሚያስተዳድሯቸው ቦታዎች ማለትም ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኑ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች በሚያስደነግጥ መልኩ ከ20 በላይ በውይይት ላይ ባሉ መስጂዶች ላይ ፈረሳ አካሂዷል ለዚህም ምንም ይቅርታ ሳይጠይቅ መቅረቱ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አስቆጥቷል። በአጠቃላይ የጥቅም ኢትዮጵያዊነት ፣አማራ ጠል የኦሮሞ ብሄርተኝነት የቱለማ Elite መገለጫ ሆነው እናገኛቸዋለን።